ዘርፎች

የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ:

አቶ ሙሉቀን ዮናስ

image description

የስራ ሂደቱ ትኩረት በከተማችን የተከሰቱ ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤና በሰውና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት በመለየት ይህንኑ ለመከላከል የሚያስችሉ ስትራተጂዎችን በመቀየስ መርሀ ግብሮች በማዘጋጀት ከሚለከታቸው አካላት ጋር መተግበር ነው፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እስትራቴጂ መተግበርና ከተማዋ  ያለምአቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዞችን ለመቀነስ የገባችውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል፡፡  በዚሁ የስራ ሂደት የሙቀት አማቂ ጋዞችን የመለካትና የመቀነሻ ስልቶችን መንደፍ፤ ለየአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ የህበረተስብ ክፍሎችን ተጋላጭነት ደረጃ መዳሰስና ተፅዕኖውን ለመቋቋም ያላቸውን አቅም ለማወቅ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት በማካሄድና በቅደም ተከተል በመደገፍ፣  ለአየር ንብረት ለውጥ ስራ ውጤታማነት ሀብት ለማፈላለግ የሚረዱ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ማዘጋጀትና አፈጻጸም መከታተል፣  በዘርፉ ድርሻ ያላቸውን የሴክተር መ/ቤቶችን በማስተባበርና በመደገፍ፤ በየዘርፉና በየደረጃው ግንዛቤ የመፍጠርና ሥልጠናዎችን የመስጠት ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ የአየር ንብረት ለውጡን ለመከላከልም ሆነ ለማጣጣም ችግር ፈቺ የሆኑ አረንጓዴ ቴክኖሎዎችን በማፈላለግ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የሙከራ ትግበራ በማካሄድና መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋት ውጤታማነቱን የመገምገም ሥራዎች የሚያከነውን ስራ ሂደት ነው፡፡

የሥራ ሂደቱ ታዳሽና አማራጭ የኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን የመለየት፣ የማስተዋወቅና የማስረጽ ሥራ በመስራት በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስና ከብክለት የጸዳ ኢነርጂን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ ሃይል ቆጣቢ የሆኑ የተለያዩ ምድጃዎችን፣ ባዮጋዞችን፣ ባዮፊዩሎችን፣ ቆሻሻን መልሶ የሚጠቀሙ ማክሰያዎችን፣ በጸሐይ ሃይል የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎችን የመለየት፣ ቴክኖሎጂ የማሻሻል፤ ሙከራ በማካሄድ ጥራቱን የማረጋገጥ፣ አምራቾችን በመደገፍ ህብረተሰቡ አንዲጠቀም በማድረግ በደን ላይ ሊደርስ የሚችልን ውድመት የመቀነስና በማገዶ አጠቃቀም የሚከሰት የቤት ውስጥ አየር ብክለትን የመከላከል ሥራ ይሰራል፡፡ ጥቅም ላይ በሚገኙ ቴክኖሎጂዎችም በአገልግሎት ላይ ስለሚባክነው ኢነርጂ ኦዲት ማድረግና እንዲስተካከል ማሳወቅ ይጠበቃል፡፡ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ሆነ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ለሚያከናውኑ ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ መስጠት እና መከታተል ይጠበቃል ፡፡

በዘርፉ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች:

icon

የአካባቢ ብክለት ጥናት ህግ ተከባሪነትና የአካባቢ ማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ ዳይሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ ትኩረት በከተማችን የተከሰቱ ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤና በሰውና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብ...

icon
icon

የአየርንብረት ለውጥ አማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዳሬክቶሬት

የስራ ሂደቱ ትኩረት በከተማችን የተከሰቱ ወይም ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤና በሰውና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብ...

icon